Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አራት የዓለም አየር መንገድ ሽልማቶችን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በስካይትራክስ 2022 የዓለም አየር መንገድ ሽልማት ላይ አራት ሽልማቶችን አሸነፈ።

አየር መንገዱ 11 ደረጃዎችን በማሻሻል ከዓለም ምርጥ 100 አየር መንገዶች 26ኛ ደረጃ ላይ መቀመጡም ነው የተገለጸው።

ይህም ደረጃ በዓለም ዙሪያ ባሉ የአየር መንገድ ደንበኞች በተሰጠ ድምጽ መሆኑን ከአየር መንገዱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በዚህም አየር መንገዱ ለአምስት ተከታታይ ዓመታት የ2022 የአፍሪካ ምርጥ አየር መንገድ፣ ለአራት ተከታታይ ዓመታት የአፍሪካ ምርጥ የቢዝነስ ደረጃ አየር መንገድ፣ ለአራት ተከታታይ ዓመታት የአፍሪካ ምርጥ የምጣኔ ሀብት ደረጃ አየር መንገድ እንዲሁም በአፍሪካ ውስጥ ምርጥ የቢዝነስ ክላስ ምግብ አቅራቢነትን አሸንፏል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.