Fana: At a Speed of Life!

ከ151 ሚሊየን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ151 ሚሊየን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዙን ጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ኮሚሽኑ ከመስከረም 6 እስከ 12 ቀን 2015 ዓ.ም ባደረገው ክትትል 144 ነጥብ 1 ሚሊየን የገቢ እና 7 ነጥብ 1 ሚሊየን ብር በላይ የወጪ ኮንትሮባንድ እቃዎች መያዙን አስታውቋል፡፡

በአጠቃላይ 151 ሚሊየን 287 ሺህ ብር ግምት ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎቹ በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች መያዛቸውም ተገልጿል፡፡

የገቢ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር ረገድ ቀዳሚዎቹ አዳማ፣ ሞያሌ እና አዋሽ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ሲሆኑ÷ በቅደም ተከተላቸው 34 ነጥብ 5 ሚሊየን፣ 28 ነጥብ 1 ሚሊየን እና 21 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የኮንትሮባንድ እቃዎችን ይዘዋል፡፡

ከተያዙት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል÷ አልባሳት፣ ነዳጅ፣ የቁም እንስሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ቡና፣ መድኃኒት፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ የመዋቢያ እቃዎች የጦር መሳሪያዎች፣ ጫት፣ አደንዛዥ እጾች፣ የምግብ ዘይት እና የተለያዩ ሀገር ገንዘቦች ይገኙበታል፡፡

የኮንትሮባንድ እቃዎቹ በፍተሻ፣ በበረራና በጥቆማ የተያዙ ሲሆን÷ እቃዎቹን ሲያዘዋውሩ የተገኙ 23 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.