Fana: At a Speed of Life!

የጎፋ ብሔረሰብ “ጋዜ ማስቃላ” እና “የኦይዳ ዮኦ” በዓል በሳውላ ከተማ እየተከበረ ነው፡

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጎፋ ብሔረሰብ “ጋዜ ማስቃላ” እና “የኦይዳ ዮኦ” በዓል በጎፋ ዞን ሳውላ ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው፡፡
 
በበዓሉ የተገኙት የባህል እና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት÷ የኢትዮጵያን ታሪክና ባህል በመጠበቅ እና በማልማት ለቀጣይ ትውልድ ለማስተላለፍ የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኙ ገልጸዋል ።
 
በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር አቶ ተሰፋዬ በልጂጌ በበኩላቸው÷ የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ባህሎችንና ቅርሶችን አቀናጅቶ ማሳደግ ከተቻለ የኢትዮጵያን ብልጽግና እና አንድነት ይበልጥ ማጠናከር እንደሚቻል ጠቁመዋል፡፡
 
ኢትዮጵያን ለማሳደግ ሁሉም ዜጋ በተሰማራበት የሥራ መስክ በጋራ ውጤታማ ሥራ ማከናወን ይገባዋልም ነው ያሉት ፡፡
 
የጎፋ ዞን ዋና አስተዳደር ዶክተር ጌትነት በጋሻው÷ በዞኑ ውስጥ የሚገኙ የጎፋና የኦይዳ ብሔረሰብ የተለያዩ ባህሎችንና ቅርሶችን ለማሳደግ ከባለድርሻ አካላት ጋር የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ ብለዋል።
 
በበዓሉ ከፌዴራል እና ከክልል እንዲሁም ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት ባህልን በተመለከተ በተዘጋጀው ጽሑፍ ላይ ውይይት ተደርጓል።
 
በማቴዎስ ፈለቀ
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.