Fana: At a Speed of Life!

በሰመራ ዩኒቨርሲቲ የሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ፈተና የቅድመ ዝግጅት ሥራ ተገመገመ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን በሰመራ ዩኒቨርሲቲ ለማስፈፀም የተቋቋመው ግብረ ኃይል የቅድመ ዝግጅት ሥራውን ገምግሟል፡፡

ግምገማውን ያደረገው ከዩኒቨርሲቲው እና ከክልሉ ትምህርት ቢሮ የተቋቋመው ግብረ ኃይል ሲሆን÷ ተማሪዎች በሰላም ተረጋግተው እንዲፈተኑ ለማስቻል ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን አረጋግጧል።

በግምገማው ወቅት እንደተገለጸው፥ ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ከ8 ሺህ 100 በላይ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያና የዩኒቨርስቲ የመግቢያ ፈተና ተፈታኞች በትምህርት ሚኒስቴር ተመድበውለታል፡፡

ፈተናውን ለማስፈፀም የሚያስፈልጉ ዝግጅቶች ቅድሚያ ተሰጥቷቸው እየተከናወኑ መሆኑም ተገምግሟል፡፡

ግብረ ኃይሉ በመስክ ምልከታ አረጋገጥኩ እንዳለው÷ ዩኒቨርሲቲው ለተፈታኞች የመፈተኛ ክፍል፣ የምግብ እና የመኝታ ክፍል አገልግሎቶች ዝግጅት በጥሩ ሁኔታ እያከናወነ ነው፡፡

የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክስ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት አብዱረህማን ከድር እንደገለጹት÷ ፈተናውን ለመስጠት ያለው ጊዜ በጣም አጭር በመሆኑ የዝጅት ሥራው በፍጥነት እንዲጠናቀቅ አሳስበዋል፡፡

ዝግጅቱ ለተፈታኞች ምቹ ሁኔታን መፍጠር በመሆኑ ኃላፊነት ወስዶ በትኩረት መሥራት እንደሚገባም በውይይቱ መገለጹን የዩኒቨርሲቲው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.