Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሞ ምርምር ማህበር ምስረታ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሞ ምርምር ማህበር ምስረታ መርሐ ግብር በአዲስ አበባ ኢሊሊ ሆቴል እየተካሄደ ይገኛል።

ማህበሩ የኦሮሞን ህዝብ ታሪክ፣ ባህል፣ ቋንቋ እና የገዳ ስርዓት በጥልቀት በመመርመር ህዝቡ ባህሉን እንዲያውቅ ለማድረግ የተቋቋመ መሆኑ ተገልጿል።

ማህበሩ የኦሮሞን ህዝብ በተመለከተ የተጻፉ መጻሕፍትን በማሳተምና በማሰራጨት ተደራሽ እንዲሆኑ የሚሰራ ይሆናል ተብሏል።

በማህበሩ ምስረታ መርሐ ግብሩ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳን ጭምሮ የፌዴራልና የክልል አመራሮች፣ አባገዳዎች ፣ ሀደ ሲንቄዎች፣ ባለሃብቶች እና የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ ባለስልጣናት እና ኮሚሽነሮች ተገኝተዋል።

በመራኦል ከድር

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.