Fana: At a Speed of Life!

የሥራ ዕድል ፈጠራና ክህሎት የልማት ሥራዎች ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ስብራቶችን ማከም ይጠበቅባቸዋል-ሙፈሪሃት ካሚል

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 21 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሥራ ዕድል ፈጠራና ክህሎት ልማት ሥራዎች ለዜጎች የሥራ ዕድልን ከማመቻቸት ባሻገር ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ስብራቶችን ማከም እንደሚጠበቅባቸው የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ተናገሩ፡፡

“ኢትዮጵያ በአዲስ ምዕራፍ፣ በአዲስ እሳቤ ላይ ትገኛለች” ያሉት ሚኒስትሯ፥ ይህን አዲስ እሳቤ ለማሰጨበጥ የሚያስችል ስልጠና በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አዘጋጅነት ከተለያዩ ክልሎች ለተውጣጡ የፖሊ-ቴክኒክ ዲኖች ከዛሬ ጀምሮ ሰልጠና በመሰጠት ላይ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

ሚኒስትሯ “አዲስ እሳቤ ለዘላቂ ጉዞ“ በሚል ርዕስ ባቀረቡት ገለፃ÷“በራሳችን ነባራዊ ሁኔታ፣ ወግ፣ልምድና ሀቅ ላይ የተመሰረተ አዲስ መንገድ እየሞከርን ነው“ ብለዋል ፡፡

“በትብብርና በመተጋገዝ ሀገርን መምራት፣ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርምን ቀርፆ ብዙ ርቀት መጓዝና ማህበራዊ እሴቶችን በመኮትኮት የአስተሳሰብ ለውጥን ማስፈን እንደሚቻል በለውጡ ሂደት በሚገባ ለመገንዘብ ችለናል“ ነው ያሉት ሚኒስትሯ፡፡

ለውጡ ይዟቸው የመጡ ተስፋዎችም እንደ ሀገር ፀንቶ ለመቆም የሚያግዙ መሰረቶች መሆናቸውንም ማአብራርተዋል።

የተለወጠው አዲስ እሳቤ በተለወጠ ሀሳብ፣ በአዲስ መዋቅራዊና ተቋማዊ ቅርፅ፣ በተለወጠ ፖሊሲና ስትራቴጂ እንዲሁም በእያንዳንዱ ዜጋ ላይ በሚስተዋል ሥነ ባህሪ ለውጥና በተግባር በሚታይ ውጤት የሚለካ ሊሆን እንደሚገባ ማስረዳታቸውንም ከሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በአዲሱ እሳቤ የሥራ ዕድል ፈጠራና ክህሎት ልማት ሥራዎች ለዜጎች የሥራ ዕድልና ከማመቻቸትና ክህሎታቸውን ከማበልፀግ ባሻገር የኢኮኖሚና የፖለቲካዊስብራቶችን በማከም፣ የኢኮኖሚውን ቀጣይነትና ዘላቂነት እውን ማድረግም ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.