Fana: At a Speed of Life!

ለሀገራዊ ምክክሩ ስኬታማነት እኛ ሚናችንን ልንወጣ ይገባል – የሀገር ሽማግሌዎች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀገራዊ ምክክሩ ውጤታማ እንዲሆን የሚጠበቅብንን ሚና በአግባቡ ልንወጣ ይገባል ሲሉ የሀገር ሽማግሌዎች ተናገሩ፡፡

የወላይታ እና የጋሞ አባቶች አዳነ አይዛ እና አቶ ተዘራ ሸዋዬ ÷ ሀገራዊ የምክክር ሂደቱ ስኬታማ እዲሆን የሀገር ሽማግሌዎች ኃላፊነታችንን መወጣት አለብን ብለዋል፡፡

ምክክሩ በሰከነ መንፈስና በቅንነት ይካሄድ ዘንድም ኃላፊነታችንን በአግባቡ መወጣት አለብን ነው ያሉት፡፡

በልዩነቶች መካከል መደማመጥ እና መቀራረብ እንዲፈጠር የሚደረጉ ጥረቶች ደግሞ ዋጋቸው ከፍ ያለ መሆኑን በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡

ወጣቱ በማስተዋል እንዲንቀሳቀስ ከመምከር ጀምሮ ለሀገሩ ዘብ እንዲሆን ማበረታታት እንደሚጠበቅም አንስተዋል።

ፖለቲከኞችም በሰከነ የፖለቲካ ዐውድ ውስጥ ሆነው ሀገርና ሕዝብን ያስቀደመ አካሄድን እንዲከተሉ በመምከር ጠንካራ ሥራዎችን እውን ሊያደርጉ ይገባል ብለዋል የሀገር ሽማግሌዎቹ፡፡

አባገዳ ቶሎሳ ሰይፈ እና ገዳ ቱፋ በበኩላቸው÷ የማኅበረሰብ መሪዎች እና የሀገር ሽማግሌዎች ችግሮች በምክክር መፈታት እንደሚችሉ በአግባቡ ማስረዳት እና በቃት መሥራት እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡

ነገሮች በስክነት ተከናውነው እርቅና ሰላም እንዲሰፍን በማገዝ ረገድ የሀገር ሽማግሌዎቹ ሚና ሊገለጥ እንደሚገባ በአጽንዖት ገልጸዋል፡፡

በአወል አበራ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.