Fana: At a Speed of Life!

ዶክተር ሊያ ከግሎባል አሊያንስ ቫክሲን ኢኒሼቲቭ ዋና ሥራ አስኪያጅ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ከግሎባል አሊያንስ ቫክሲን ኢኒሼቲቭ ዋና ስራ አስኪያጅ ዶክተር ሲዝ በርክሌይ ጋር በክትባት አገልግሎት እና ተዛማጅ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ፡፡

በውይይታቸውም በዋናነት ስላልተከተቡ ሕጻናት (ዜሮ ዶዝ)፣ በመጪው ጊዜ ስለሚካሄደው የኩፍኝ ክትባት ዘመቻ፣ የመረጃ አያያዝና ማሻሻል ሥራ እንዲሁም የኮቪድ ክትባት ስርጭት እና ስለሂዩማን ፓፒሎማ ቫይረስ ክትባት መክረዋል፡፡

ሚኒስቴሩ የጤና መረጃ ጥራት ማሻሻል፣ የኤሌክትሮኒክስ መረጃ አያያዝ ማዘመንና ማስፋት፣ የባለሙያዎችን አቅም ማጎልበት እና የመጀመሪያ አሃድ ጤና አገልግሎት ማጠናከር ላይ በትኩረት እየሠራ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በግጭት ውስጥ ላሉ፣ ለተጎዱና ለተፈናቀሉ የማህበረሰብ ክፍሎች የክትባት አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ ከአጋር አካላት ጋር እየተሠራ መሆኑንም ዶክተር ሊያ አስረድተዋል፡፡

ዶክተር ሲዝ በርክሌይ በበኩላቸው ኢትዮጵያ የረጅም ጊዜ ትልቅ አጋር መሆኗን አንስተው በኮቪድ19 እና ጤና ኤክስቴንሽን ላይ የተሠራው ሥራ አመርቂ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በተለያየ ምክንያት ያልተከተቡ ሕጻናትንተደራሽ ማድረግን፣ መደበኛ የክትባት አገልግሎትን ማጠናከር ላይ ተጠናክሮ እንደሚሠራ ያላቸውን እምነት ገልጸው÷ ለመደገፍም ዝግጁነታቸውን አረጋግጠዋል፡፡

በውይይቱ ላይ የዓለም ጤና ድርጅት እና ዩኒሴፍ ተወካዮች መገኘታቸውን የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.