Fana: At a Speed of Life!

የአዳሚቱሉ የፀረ አረምና ተባይ ፋብሪካ በሙሉ አቅሙ እንዲያመርት ድጋፍ ይደረጋል-ኢንጅነር ታከለ ኡማ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዳሚቱሉ የፀረ አረምና ተባይ ፋብሪካ በሙሉ አቅሙ ማምረት እንዲችል አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ የማዕድን ሚኒስትሩ ታከለ ኡማ ገለጹ፡፡

ኢንጂነር ታከለ ኡማ እና የግብርና ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ድሪባ ኩማ የአዳሚቱሉ የፀረ አረምና ተባይ ፋብሪካን ጎብኝተዋል፡፡

ኢንጂነር ታከለ ጉብኝቱን አስመልከተው በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ፋብሪካው በአይነት ከ20 በላይ ምርቶችን ለገበያ እያቀረበ እንደሚገኝ ጠቁመው÷ ለግብርናው ክፍለ ኢኮኖሚ ትልቅ አቅም እንዳለው ገልጸዋል፡፡

ይሁን እንጅ ፋብሪካው አሁን ላይ በተለያዩ ችግሮች ምክንያት ከማምረት አቅሙ 20 በመቶ ብቻ እያመረተ ነው ብለዋል፡፡

ለዚህ ደግሞ የግብዓት እጥረት ዋና ችግር መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

በመሆኑም በቅርብ ጊዜ ችግሩ ተፈትቶ ፋብሪካው በሙሉ አቅሙ ማምረት እንዲችል አስፈላጊው ድጋፍ ይደረጋል ብለዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.