Fana: At a Speed of Life!

ሊግ ኩባንያው በኢትዮጵያ መድን፣ ድሬዳዋ እና ወልቂጤ ከተማ ላይ የቅጣት ውሳኔ አሳለፈ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2015 (ኤፍ ቢሲ) ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኩባንያ በ2015 ዓ.ም በ1ኛ ሳምንት ውድድሮች ላይ በታዩ የሥነ ምግባር ግድፈቶች ላይ ውሳኔ አሳለፈ፡፡

የሊግ ኩባንያው ውድድር አመራርና ሥነስርዓት ኮሚቴ ባደረገው ስብሰባ በሳምንቱ በተደረጉ ጨዋታዎች ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የሥነ ምግባር ሪፖርት ከመረመረ በኋላ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል።

በዚህም መሰረት ኤልያስ አህመድ (ድሬደዋ ከተማ) ዳኛን አፀያፊ ስድብ በመሳድብ ሪፖርት የቀረበበት ሲሆን ለፈፀመው ጥፋት በፌዴሬሽኑ ሥነ ምግባር መመሪያ መሰረት ሶስት ጨዋታ እንዲታገድና በተጨማሪም ሶስት ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት እንዲከፍል ተወስኗል፡፡

እንዲሁም ጊት ጋትኩት (ሲዳማ ቡና) ፣ ሽመክት ጉግሳ (ፋሲል ከነማ) ፣ ዊሊያም ሰለሞን(አዳማ ከተማ) ሁለተኛ ቢጫ ካርድ የሚያሰጥ ጥፋት በመፈፀም በቀይ ካርድ ከሜዳ በመውጣታቸው 1 ጨዋታ እንዲታገዱ ተወስኗል፡፡

በክለብ ደረጃ ድሬደዋ ከተማ በሳምንቱ ጨዋታ የክለቡ አምስት ተጫዋቾች ካርድ ማየታቸውን ተከትሎ በመሆኑ ክለቡ 5 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት እንዲከፍል ተወስኖበታል፡፡

ኢትዮጵያ መድን ባደረገው ጨዋታ ከዕረፍት መልስ የክለቡ ተጫዋቾች 4 ደቂቃ ወደ ሜዳ ዘግይተው ስለመግባታቸው ሪፖርት በመደረጉ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የውድድር ደንብ ክፍል መሰረት ክለቡ 15 ሺህ ብር እንዲከፍል ተወስኗል፡፡

ወልቂጤ ከተማ ባደረገው የሳምንቱ ጨዋታ የክለቡ ተጫዋች ሳሙኤል አስፈሪ ከተፈቀደው የመለያ ቁጥር ውጪ መለያ ለብሶ ስለመጫወቱ ሪፖርት የተደረገበት በመሆኑ በውድድር ደንቡ መሰረት ክለቡ 3 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት እንዲከፍል የተወሰነበት መሆኑን ከሊግ ኩባንው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.