Fana: At a Speed of Life!

ለመከላከያ ሠራዊት 12 ሚሊየን ብር የሚገመት ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣ 2015 (ኤፍ ቢሲ) በአማራ ክልል አዊ ብሄረሰብ አስተደደር ፣ ምስራቅ ጎጃም ዞን እና በጋምቤላ ክልል ማጃንግ ብሄረሰብ ዞኖች ለመከላከያ ሠራዊት 12 ሚሊየን ብር የሚገመት የዓይነት ድጋፍ አድርገዋል፡፡

የምስራቅ ጎጃም ዞን ለኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ከ6 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የእርድ እንስሳቶችና 175 ኩንታል በሶ ድጋፍ ማድረጉን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ዞንም ለመከላከያ ሰራዊት 4 ሚሊየን ብር የሚገመት ድጋፍ ያደረገ ሲሆን፥ በድጋፉም የእርድ እንስሳትን ጨምሮ ምግብና ቁሳቁስ አበርክቷል።

በአዊ ዞን የተደረገው ድጋፍ ለሦስተኛ ጊዜ መሆኑ የተጠቀሰ ሲሆን፥ በቀጣይም ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የአሚኮ ዘገባ አመለክቷል፡፡

የጋምቤላ ክልል በበኩሉ ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ሲያደርግ ለሁለተኛ ጊዜው ሲሆን፥ በአሁኑ በማጃንግ ብሄረሰብ ዞን በኩል የሁለት ሚሊየን ብር ግምት ያላቸው የቁም ከብቶች ድጋፍ በማድረግ የሀገር ደጀንነቱን ተገልጿል፡፡

በትዕግስት አስማማው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.