Fana: At a Speed of Life!

ግብርና የኢኮኖሚያችን መነሻ ፤ የእድገታችን መዳረሻ ነው-ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 6 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)ግብርና የኢኮኖሚያችን መነሻ፤ የእድገታችን መዳረሻ ነው ሲሉ የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ ተናገሩ፡፡

ርእሰ መስተዳድሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ÷ግብርና የኢኮኖሚያችን መነሻ፤ የእድገታችን መዳረሻ ነው፤የግብርናውን ምርታማነት ማሳደግ የዜጎችን የኑሮ ደረጃ ማሻሻል እና የአገርን እድገትና ብልጽግና ማረጋገጥ ነው ብለዋል።

የዘርፉን ውጤታማነት በተፈለገው ደረጃ በማሻሻል እንደሀገር ድህነትን መቀነስ ብቻ ሳይሆን የስንዴ ተመጽዋችነት ታሪካችንን በአጭር ጊዜ መቀየር የምንችልበት አቅም እየፈጠርን ነው ሲሉም ተናግረዋል።

የምግብ ዋስትናችንን ከማረጋገጥ በተጨማሪ ወደ ኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ የምናደርገውን ጉዞም እናፋጥናለን ያሉት ርእሰ መስተዳድሩ የሞረትና ጅሩ ወረዳ አርሶ አደሮች በኩታ ገጠም እያለሙት ያለው የስንዴ ሰብል ልማት በምግብ እህል ራሳችንን እንደምንችል አንዱ ማሳያ ነው ብለዋል።

ይህንን ውጤት አጠናክሮ ለማስቀጠል በየደረጃው የምንገኝ የዘርፉ አመራሮች፣ ተቋማትና ባለድርሻ አካላት ርብርብ ማድረግ ይኖርብናል ሲሉም ገልፀዋል።

እንዲሁም በግብርና ልማት የተገኙ መልካም ተሞክሮዎችን ለማስፋት እና የዘርፉን ውጤታማነት ለማሻሻል የሚደረገው ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.