Fana: At a Speed of Life!

የምዕራባውያንን ያልተገባ ጣልቃ ገብነት የሚቃወም ህዝባዊ ሰልፍ በአዲስ አበባ ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 12 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ”ለኢትዮጵያ እቆማለሁ ድምጼን አሰማለሁ” በሚል መሪ ቃል የምዕራባውያንን ያልተገባ ጣልቃ ገብነት የሚቃወም ህዝባዊ ሰልፍ በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ተካሄደ።

ህዝባዊ ሰልፉን የሙያ ማህበራት፣ የሲቪክ ማህበራት እና የፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ ያዘጋጁት ነው ተብሏል፡፡

የሰልፉ ዋና ዓላማ ኢትዮጵያ ያለችበትን ወቅታዊ ሁኔታ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማሳወቅና ለሀገሪቱ ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት መከበር በሁሉም መስክ ከመንግስት ጎን መቆማችንን ለማረጋገጥ ነው ሲሉ የሰልፉ አዘጋጆች ገልፀዋል፡፡

በሰላማዊ ሰልፉ ምዕራባውያን በአሸባሪው ሕወሓት ላይ የያዙትን የተለሳለሰ አቋም እና በኢትዮጵያ ላይ እያደረጉት ያለውን ጫና የሚቃወሙ መልዕክቶች ተላልፈዋል።

የምዕራባውያን ሀገራትና የዓለም አቀፍ ተቋማት ባለስልጣናት በኢትዮጵያ ዙሪያ የሚያስተላልፉትን የተሳሳተ መልዕክት የሚቃወሙ መልዕክቶችም ተስተጋብተዋል።

ሰልፉ አሸባሪው ህወሓት የቀረበለትን የሠላም አማራጭ ወደ ጎን በመተው ለ3ኛ ጊዜ የጀመረውን አስገዳጅ ጦርነት ለመቀልበስና የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እያደረገ ላለው ተጋድሎ በሁለንተናዊ ድጋፍ ህዝቡ ደጀንነቱን ያሳየበት ነው።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.