Fana: At a Speed of Life!

አቶ መላኩ አለበል እና በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር በአምራች ዘርፍ የተሰማሩ የቻይና ኢንዱስትሪዎችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል እና በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዣኦ ዡዩአን በአምራች ዘርፍ የተሰማሩ የቻይና ኢንዱስትሪዎችን ጎበኙ።

ጉብኝቱ ኢንዱስትሪዎቹ እያጋጠሟቸው ያሉ ችግሮችን በአካል ተመልክቶ ማነቆዎችን ለመለየት ያለመ መሆኑ ተመላክቷል።

እንዲሁም አሁን ያሉትን የማስፋት እና ያሉ መልካም እድሎችን ማሳየት መሆኑ ተገልጿል።

የኢትዮጵያና ቻይና የሁለትዮሽ ግንኙነትን በአምራች ዘርፉ ማጠናከርም የጉብኝቱ አላማዎች መሆናቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ኢንዱስትሪዎቹ የገጠማቸውን ተግዳሮቶች ለመፍታት ከጉብኝቱ በኋላ በሚደረግ ውይይት የመፍትሄ አቅጣጫዎች እንደሚቀመጡ በጉብኝቱ መርሐ ግብር ተመላክቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.