Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የሠላም ንግግሩ ውጤት ኢትዮጵያን ወደፊት ለማራመድ ትልቅ ፋይዳ ያለው መሆኑን ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ በደቡብ አፍሪካ የተፈረመው ሥምምነት ኢትዮጵያን ወደፊት ለማራመድ ትልቅ ፋይዳ ያለው መሆኑን ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በመግለጫቸው ÷ ስምምነቱ ከአራት ዓመት ተኩል በፊት ወደ ተጀመረው የለውጥ ጎዳና የሚወስድና ለሰላም ያለንን ቁርጠኝነት ያሳየ እና ጸንቶ የሚኖር ነው ብለዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፥ “እኛም ለተግባራዊነቱ ያለን ቁርጠኝነት ጠንካራ ነው” ሲሉም ነው የገለጹት፡፡

 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፥ ለአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን እና ለአፍሪካ ኅብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ለቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ፣ ከሠላም አባላቱ ጋር እንዲሁም በሠላም ንግግሩ ላይ ለተሳተፉ ከፍተኛ ተወካዮች ፣ ለቀድሞው የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እና ለቀድሞ የደቡብ አፍሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ፉሙዚሌ ማላምቦ ፣ እንዲሁም የአፍሪካ ኅብረት መርኅ የሆነውን “ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ ፍትሔዎች” የሚለውን አቋም ለመሩት የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማትን በኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ሥም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.