ፕሬዚዳንት ሳኅለወርቅ ዘውዴ ከኮቲዲቯር ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ
በተመሳሳይ ፕሬዚደንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ÷ የአፍሪካ ልማት ባንክ በአቢጃን ኮቲዲቯር በተዘጋጀው የአፍሪካ ኢንቨስትመንት ፎረም ላይ ተሳትፈዋል፡፡
በችግር ጊዜ መልካም አጋጣሚዎች መኖራቸውን የጠቀሱት ፕሬዚዳንቷ÷ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በባንኩ ድጋፍ በስንዴ ምርት በኢትዮጵያ ስለተገኘው ውጤት አብራርተዋል፡፡
ኮቲዲቯር በተመድ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ለኢትዮጵያ ለሰጠችው ድጋፍ ማመስገናቸውን የፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-