Fana: At a Speed of Life!

የጣና በለስ-ጃዊ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ጥገና ተጠናቆ ዛሬ ኃይል መሥጠት ይጀምራል

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 26 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በስርቆት ወንጀል ሳቢያ ለአንድ ሳምንት ኃይል መሥጠት ያቋረጠው የጣና በለስ- ጃዊ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ጥገና መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል፡፡

የሰሜን ምዕራብ ሪጅን የማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኦፕሬሽን መምሪያ ዳይሬክተር አቶ ውበት አቤ እንደገለጹት ÷ ኃይል መሥጠት ከጀመረ ገና ሁለት ዓመት እንኳ ያልሞላው የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመርሩ ላይ ከፍተኛ የሆነ የስርቆት ወንጀል ተፈፅሞበት ነበር፡፡

የስርቆት ወንጀል የተፈጸመበት ቦታ ተራራማ በመሆኑም የጥገና ሥራውን ፈታኝ አድርጎት እንደነበር ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡

የስርቆት ወንጀል ፈፅመዋል ከተባሉት ተጠርጣሪዎች የተወሰኑትን ከክልሉ የመሠረተ ልማት አካላት እንዲሁም ከዞን እና ከወረዳ አመራሮች ጋር በመነጋገር በቁጥጥር ሥር ማዋል መቻሉንም ነው የተናገሩት።

የጥገና ቡድኑ አስተባባሪ አቶ አምባው ጋሻው በቡኩላቸው ÷ በኃይል ተሸካሚ ምሰሦዎች ላይ የነበሩ ከ150 እስከ 200 የሚደርሱ የመወጣጠሪያ ብረቶች ላይ ስርቆት መፈፀሙ በፍተሻ ሥራ መረጋገጡን ጠቁመዋል፡፡

ለአንድ ሳምንት ኃይል መሥጠት አቋርጦ የነበረው የጣና በለስ- ጃዊ ባለ132 ኪሎ ቮልት የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ጥገናው ተጠናቆ ዛሬ ኃይል መሥጠት እንደሚጀምርም መናገራቸውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል መረጃ ያመላክታል፡፡

ኅብረተሰቡ በከፍተኛ ወጪ ተገንብተው አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ የብረት ምሰሶዎችና ሽቦዎችን ከመሰል ዝርፊያዎች እንዲጠብቅም ጥሪ አቅርበዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.