Fana: At a Speed of Life!

ዓለም አቀፍ የማዕድን ኤክስፖ ከሕዳር 1 እስከ ሕዳር 3 ቀን ድረስ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፍ የማዕድን ኤክስፖ “Mintex” ከሕዳር 1 እስከ ሕዳር 3 ቀን 2015 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ ይካሄዳል፡፡

የማዕድን ሚኒስትር ታከለ ኡማ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ በኤክስፖው ከ270 በላይ የሀገር ውስጥና የውጪ ኩባንያዎች ይሳተፋሉ፡፡

የማዕድን ኩባንያዎች፣ የጌጣጌጥ አምራቾችና ላኪዎች፣ የማዕድን ቴክኖሎጂ አምራቾችና አስመጪዎች እንዲሁም የፋይናንስ ተቋማት ይሳተፋሉ፡፡

በዚህም አገልግሎታቸውን በቀጥታ ለሀገር ውስጥና ለውጪ ሸማቾች እንደሚያስተዋውቁ ተገልጿል፡፡

ከውጪ የሚመጡ የማዕድን ኩባንያዎች በኤክስፖው ላይ መሳተፋቸው÷ በሀገራችን ያለውን የማዕድን የኢንቨስትመንት አማራጭ እንዲመለከቱና በዘርፉ መዋዕለ-ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ዕድል ይጥል ብለዋል ኢንጂነር ታከለ፡፡

በማዕድን ዘርፉ ላይ ትኩረት ያደረጉ የቴክኖሎጂ አምራቾች መሳተፋቸውም÷ የሀገራችን የማዕድን ዘርፍ አዳዲስ የቴክኖሎጂ አማራጮችን እንዲተዋወቅ መልካም አጋጣሚ ይፈጥራል ነው ያሉት፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.