Fana: At a Speed of Life!

ዓሊ ቢራ የነጻነት፣ የእኩልነትና የእውነተኛ ወንድማማችነት ድምጽ ነው – አቶ ሽመልስ አብዲሳ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓሊ ቢራ የነጻነት፣ የእኩልነትና የእውነተኛ ወንድማማችነት ድምጽ ነው ሲሉ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ገለጹ፡፡

የአርቲስት ዓሊ ቢራ አስከሬን የሽኝት ሥነ ስርዓት በወዳጅነት ዐደባባይ እየተካሔደ የሚገኝ ሲሆን ፥ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በመልዕክታቸውም ፥ ዓሊ ቢራ በኢትዮጵያ ስድስት ቋንቋዎች ያዜመና ባህል ያስተሳሰረ ባለሙያ መሆኑን አንስተዋል፡፡

በዚህም ስለኢትዮጵያ በጽናት የታገለ፣ ከፍተኛ መስዕዋትነት የከፈለና ሁልጊዜም በተስፋ የሚኖር፣ በተገኘው ነገር ላይ የሚጨምር አርቆ አሳቢ የፍቅር ሰው ነው ብለዋል ርዕሰ መስተዳድሩ፡፡

በህመም ላይ እያለም ስለሀገሩና ስለህዝቡ የሚጨነቅ አርበኛ ሰው ነበር ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ፥ ኢትዮጵያ ትልቅ ሰው ብታጣም ለሀገር መሰረት የሚሆኑ ታላላቅ ስራዎችን ሰርቶልናል ነው ያሉት፡፡

ዓሊ የሀገር እድገት፣ የህዝቦች ነጻነትና እኩልነት በትምህርት ውስጥ እንዳለ የሚረዳ ሰው መሆኑን አንስተው ፥ በዚህ ትዝታ ውስጥ ሆነን ሀገርን የመገንባት ኃላፊነት አለብን ብለዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.