የሐረሪ ክልል ካቢኔ የክልሉን የመጀመሪያ ሩብ አመት እቅድ አፈፃፀም እየገመገመ ነው
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የሐረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት(ካቢኔ) በክልሉ በመጀመሪያዎቹ ሶስት ወራት የተከናወኑ ተግባራትን እየገመገመ ይገኛል።
በግምገማው የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ÷ በክልሉ ከፕሮጀክቶች አፈፃፀም ጋር በተያያዘ እየተከናወኑ የሚገኙ አበረታች ስራዎችን ማጠናከር እንደሚገባ ጠቁመዋል።
እንዲሁም የዓለም ቅርስ የሆነውን የጁገል ቅርስን ጠብቆ ለትውልድ ከማስተላለፍ አንፃር አበረታች ስራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውንም ማንሳታቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በመድረኩም በክልሉ የሚገኙ የሴክተር መስሪያ ቤቶች በመጀመሪያው ሩብ አመት ያከናወኗቸውን ተግባራት በሚመለከት ሪፖርት እያቀረቡ ሲሆን ÷ካቢኔውም በሪፖርቶቹ ላይ በመምከርም አቅጣጫ ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል።