Fana: At a Speed of Life!

ለተፈናቀሉ ወገኖች ከ10 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የአልባሳት ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 1 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ተፈናቅለው ለሚገኙ ወገኖች ከ10 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው የአልባሳት ድጋፍ አደረገ።

ሚኒስቴሩ 16 ሺህ 124 የተለያዩ አልባሳትና ብርድ ልብሶች ድጋፍ ለዞኑ የሴቶች፣ ሕጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ አስረክቧል።

ሚኒስቴር መስሪያቤቱ በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ አደጋዎች ለተፈናቀሉ ወገኖች የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደርግ መቆየቱንና ይሄንኑ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

የዞኑ የሴቶች፣ ሕጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ ወይዘሪት ካባ ሲሳይ በበኩላቸው÷ ሚኒስቴሩ ላደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበው የተፈናቀሉ ወገኖች ወደቀያቸው ተመልሰው እስኪቋቋሙ ድረስ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ድጋፋቸውን እንዲያጠናክሩ መጠየቃቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.