Fana: At a Speed of Life!

ኖርዌይ በአካባቢ ጥበቃ ከኢትዮጵያ ጋር  ያላትን አጋርነት አጠናክራ እንደምትቀጥል ገለፀች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኖርዌይ በአካባቢ ጥበቃና የአየር ንብረት ለውጥ መከላከል ጉዳዮች ከኢትዮጵያ ጋር   ያላትን አጋርነትና አብሮነት አጠናክራ እንደምትቀጥል ገለፀች፡፡

የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዶክተር  ፍጹም አሰፋ አዲስ ከተሸሙት በኢትዮጵያ የኖርዌይ አምባሳደር ስቴይን ክሪስቴንሰን ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸው ሚኒስትሯ ÷ኖርዌይ የኢትዮጵያ የረጅም ጊዜ የልማት አጋር መሆኗን በማድነቅ ይህም አጋርነት በዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ በአካባቢ ጥበቃና የዓየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል ያቀደቻቸውን  ስትራቴጂዎችና ፕሮግራሞች ማብራራታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

አምባሳደር  ስቴይን   በበኩላቸው÷ አገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር በብዙ ጉዳዮችና ፕሮግራሞች በተለይም በአካባቢ ጥበቃና የአየር ንብረት ለውጥ መከላከል ጉዳዮች አጋርነቷንና አብሮነቷን አጠናክራ እንደምትቀጥል ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልፀዋል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.