Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮ- ኬንያ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር በይፋ የኤሌክትሪክ ሽያጭ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮ- ኬንያ ባለ 500 ኪል ቮልት የኃይል ማስተላለፊያ መስመር እና የኮንቨርተር ማከፋፈያ ጣቢያ ዛሬ በይፋ የኤሌክትሪክ ሽያጭ ጀምሯል፡፡

ዛሬ በይፋ ኃይል ማስተላለፍ የጀመረው የኢትዮ – ኬኒያ ባለ 500 ኪል ቮልት የማስተላለፊያ መስመር በዓመት እስከ 100 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ገቢ የማስገባት አቅም ያለው ነው ተብሏል፡፡

እንዲሁም ከኬንያ አልፎ ከታንዛኒያ እስከ ደቡብ አፍሪካ ላሉት ሀገራት እስከ 2ሺህ ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ የማስተላለፍ አቅም ያለው መሆኑ ተገልጿል፡፡

ኢትዮጵያ ቀደም ብላ ከሱዳን እና ከጅቡቲ ጋር የኃይል ሽያጭ የጀመረች ሲሆን፥ ከሶማሌ ላንድ፣ ታንዛኒያ፣ ደቡብ ሱዳን እና ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ጋር የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ለማከናወን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርማለች።

በዚህም ባለፈው ዓመት ለሱዳን እና ለጅቡቲ ከቀረበ የኤሌክትሪክ ኃይል 95 ነጥብ 4 ሚሊየን የአሜሪካ ዶሊር ገቢ መገኘቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ለፋና ብሮድካቲንግ ኮርፖሬት የላከው መግለጫ ጠቁሟል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.