በፕሪሚየር ሊጉ ባሕርዳር ከተማ እና ድሬዳዋ ከተማ ድል ቀንቷቸዋል
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 9፣2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች ተካሄደዋል።
10 ሰአት ላይ በተደረገ የመጀመሪያው ጨዋታ ባሕርዳር ከተማ ኢትዮጵያ ቡናን 3 ለ 1 አሸንፏል፡፡
ፉአድ ፈረጃ፣ ፍፁም ጥላሁን እና ያሬድ ባየህ የባሕርዳርን ጎሎች ሲያስቆጥሩ ብቸኛዋን የኢትዮጵያ ቡና ጎል ሮቤል ተክለሚካኤል አስቆጥሯል፡፡
ባሕርዳር ከተማ ማሸነፉን ተከትሎ ሀድያ ሆሳዕና እና ሐዋሳ ከተማን በግብ ክፍያ በመብለጥ 3ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡
ምሽት 1 ሰዓት ላይ በተደረገ ጨዋታ ደግሞ ድሬዳዋ ከተማ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ተገናኝተዋል።
ጨዋታውን ድሬዳዋ ከተማ 2 ለ 1 ሲያሸንፍ ቢኒያም ጌታቸው እና ቻርለስ ሙሴጌ የድል ጎሎቹን አስቆጥረዋል።
ናትናኤል ሰለሞን ደግሞ የኢትዮ ኤሌክትሪክን ማስተዛዘኛ ጎል ማስቆጠር ችሏል።