Fana: At a Speed of Life!

ተቋማቱ የጋራ ዕቅድ አውጥተው በትብብር ለመሥራት ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር እና የብሔራዊ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ኢትዮጵያ ለገጠማት ሰው ሠራሽና ተፈጥሯዊ አደጋዎች ምላሽ ለመስጠት በትብብር ለመሥራት ተስማሙ፡፡

ተቋማቱ ሥራን በመከፋፈል ለመሥራት በሚያስችላቸው ጉዳዮች ላይ ከመከሩ በኋላ÷ በቀጣይ ዕቅድ አውጥተው ለመሥራት ስምምነት ላይ መድረሳቸውን አስታውቀዋል፡፡

በመሆኑም ተቋማቱ በአደጋ ምላሽ፣ በአደጋ ስጋት ቅነሳ እና በሐብት ማሰባሰብ ላይ በጋራ እንደሚሠሩ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር መረጃ አመላክቷል፡፡

በጋራ በሚሠሩ ሥራዎች ላይም የመግባቢያ ሠነድ አዘጋጅተው በአጭር ጊዜ ወደ ሥራ ለመግባት መክረዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.