Fana: At a Speed of Life!

አዲሱን የ “ኤርፖርት ሲቲ” ግንባታ በተያዘው በጀት ዓመት ለማስጀመር ዝግጅት መደረጉን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲሱን የ”ኤርፖርት ሲቲ” ግንባታ በተያዘው በጀት ዓመት ለመጀመር የሚያስችለውን ሥራ እያከናወነ መሆኑን የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው ገለጹ፡፡

ፕሮጀክቱ በአጠቃላይ 5 ቢሊየን ዶላር በጀት እንደተያዘለትና በአምስት ዓመታት ውስጥ ተገንብቶ እንደሚጠናቀቅ ተገልጿል፡፡

በኦሮሚያ ክልል ከቢሾፍቱ ከተማ ጥቂት ወጣ ባለ ሥፍራ ላይ እንደሚገነባ የተገለጸው ይህ ፕሮጀክት÷ ዘመናዊ ሆቴሎች፣ ከቀረጥ ነጻ የግብይት ሥፍራና የካርጎ ሎጂስቲክ ማዕከል ይኖረዋል ተብሏል።

አየር መንገዱ አሁን ላይ ግንባታውን ለማስጀመር ፈረንሳይ በሚገኝ አንድ ኩባንያ አማካኝነት ጥናት አካሄዶ ማጠናቀቁን አቶ መስፍን ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡

የፕሮጀክቱን ግንባታ ለማስጀመር ከኦሮሚያ ክልል ጋር በቅርበት እየተሠራ መሆኑን ጠቁመው÷ የፕሮጀክቱን ዲዛይን ለሚሠሩ ኩባንያዎች ጨረታ እንደሚወጣ እና በተያዘው ዓመት የዝግጅት ሥራዎችን በማጠናቀቅ ወደ ግንባታ ይገባል ብለዋል፡፡

ፕሮጀክቱ እንደ አስፈላጊነቱ በሁለት ምዕራፍ ተከፍሎ ሊገነባ እንደሚችልም ጠቁመዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.