Fana: At a Speed of Life!

የእንግሊዝ ፕሪሚየርሊግ ከዓለም ዋንጫ መልስ ዛሬ በሚደረጉ ጨዋታዎች ይጀመራል

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የእንግሊዝ ፕሪሚየርሊግ ከዓለም ዋንጫ መልስ ዛሬ በሚደረጉ የቦክሲንግ ደይ ጨዋታዎች ጅማሮውን ያደርጋል፡፡

ፕሪሚየር ሊጉ በኳታሩ የዓለም ዋንጫው ምክንያት ለአንድ ወር ያህል ተቋርጦ የቆየ ሲሆን ከአንድ ሳምንት እረፍት በኋላ በዛሬው እለት የሊጉ የገና ዋዜማ (ቦክሲንግ ደይ) ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡

በዚሁም መሰረት ቀን 9 ሰዓት ከ30 ብሬንትፎርድ ከቶተንሃም ሆትስፐርስ ፣ ምሽት 2 ሰዓት ከ30 አስቶንቪላ ከሊቨርፑል  እንዲሁም ምሽት 5 ሰዓት አርሰናል ከዌስትሃም ዩናይትድ የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው፡፡

ክሪስታል ፓላስ ከፉልሃም፣ ኤቨርተን ከወልቭስ፣ ሌሲስተር ሲቲ ከኒውካስትል ዩናይትድ ፣ ሳውዝሃምፕተን ከብራይተን ሌሎች ዛሬ የሚደረጉ መርሐ ግብሮች ናቸው፡፡

ሊጉን አርሰናል በ37 ነጥብ ሲመራ ማንቼስተር ሲቲ በ32 እንዲሁም ኒውካስትል ዩናይትድ በ30 ነጥብ ተከታዮቹን ደረጃዎች ይዘዋል፡፡

የማንቼስተር ሲቲው አጥቂ ኧርሊንግ ሃላንድ በ18 ጎሎች ሲመራ ሃሪ ኬን በ12 ጎሎች እንዲሁም የብሬንትፎርዱ ኢቫን ቶኒ በ10 ጎሎች ይከተላሉ፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.