Fana: At a Speed of Life!

በባሕር ዳር ከተማ በ2 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር የአስፋልት መንገድ ግንባታ ሥራ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በባሕር ዳር ከተማ በዘመናዊነት ቀዳሚ የሚሆን በ2 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር የአስፋልት መንገድ ግንባታ ሥራ ተጀምሯል።

ፕሮጀክቱ በከተማዋ ዳግማዊ ምኒልክ ክፍለ ከተማ ከመብራት ኃይል እስከ አየር መንገድ የሚደርስ ነው ተብሏል፡፡

የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ድረስ ሳህሉ፣ የአማራ ክልል ከተማ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ቢያዝን እንኳሆነና ሌሎች የክልል፣ የከተማና ክፍለ ከተማ አመራሮች የመንገድ ግንባታ ስራውን በይፋ አስጀምረዋል።

ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ድረስ ሳህሉ በመርሐ ግብሩ በከተማዋ ጥራት ያላቸው ትላልቅ መሰረተ ልማቶች እየተገነቡ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የክልሉ ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ኀላፊ አቶ ቢያዝን እንኳሆነ በበኩላቸው የከተሞች ዋነኛ የእድገት መገለጫ የመሰረተ ልማት መሟላት ነው ብለዋል።

የመንገዱ አጠቃላይ ርዝመት 8 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር ሲሆን 40 ሜትር ስፋት ይኖረዋል ተብሏል፡፡

መሰል ዘመናዊ የመንገድ ግንባታዎች በሌሎች የክልሉ ከተሞች እንዲስፋፋ በትኩረት እየተሠራ መሆኑን ከክልሉ ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.