Fana: At a Speed of Life!

አመራሩ ህዝቡን በማስተባበር የተቀናጀ የተፈጥሮ ሀብት ስራ ውጤታማ እንዲሆን በትኩረት ሊሰራ ይገባል – ር/መስተዳድር ይልቃል ከፋለ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የፖለቲካ አመራሩ ህዝቡን በማስተባበር የ2015 የተቀናጀ የተፈጥሮ ሀብት ስራ ውጤታማ እንዲሆን በትኩረት ሊሰሩ ይገባል ሲሉ የአማራ ክልል ርዕስ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ ገለጹ፡፡

ርዕስ መስተዳድሩ ይህን ያሉት የክልሉ የ2015 የተቀናጀ ተፋሰስ ልማት ስራ የማስጀመሪያ መርሐ ግብር ላይ በተገኙበት ወቅት ነው።

ለተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ተገቢው ትኩረት ሊሰጥ ይገባል ያሉት ርዕስ መስተዳድሩ ፥ ባለፉት ዓመታት የተገኙ ጥሩ ተሞክሮዎችን በማስፋት ለተግባሩ ውጤታማነት በቁርጠኝነት መስራት ይገባልም ነው ያሉት።

የአፈር መከላትን ለማስቀረትና በተፋሰሶች ህዝቡን ተጠቃሚ ለማድረግ በሚሰሩ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ስራዎች የፖለቲካ አመራሩ በንቃት ሊሳተፍ እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡

የ2015 የክልሉ የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ስራ ከዘመቻ በወጣ መልኩ በውጤት ሊታጀብ እንደሚገባ ርዕስ መስተዳድሩ አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ ኃይለማርያም ከፍያለው በበኩላቸው ፥ በተያዘው በጀት ዓመት በተቀናጀ የተፋሰስ ስራ 8 ሺህ 548 ተፋሰሶችን ለማልማት መታቀዱን ጠቁመዋል።

ለ23 ቀናት በሚቆየው የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ስራ በክልሉ 4 ነጥብ 3 ሚሊየን የህብረተሰብ ክፍሎች እንደሚሳተፉ የቢሮ ኃላፊው ገልፀዋል።

የዘንድሮው የአፈር ጥበቃና የደን ልማት ስራው በ157 ወረዳዎች እንደሚናወን ተገልጿል።

በምናለ አየነው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.