Fana: At a Speed of Life!

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እና የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር በትብብር ለመሥራት ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እና የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር በትብብር ለመሥራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ።

ሥምምነቱን የተፈራረሙት የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዋና ሥራ አሥፈጻሚ አቶ አድማሱ ዳምጠው እና የከተማና መሠረተ-ልማት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ ናቸው።

ስምምነቱ ሁለቱ ተቋማት በቀጣይ በበርካታ ዘርፎች ላይ በትብብር ለመሥራት የሚያስችላቸው ነው ተብሏል፡፡

የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አድማሱ ዳምጠው በሥምምነቱ ወቅት ÷ ሥምምነቱ ሀገሪቱ የጀመረችውን የልማት ሥራ ወደ ኅብረተሰቡ እንዲደርስ ለማድረግ ያግዛል ብለዋል።

ከከተማና መሠረተ ልማት ጋር የተያያዙ ሥራዎችንም በሙሉ ዐቅምና ፍላጎት ወደ ሕዝቡ ለማድረስ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዝግጁ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡

የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ በበኩላቸው ÷ ተቋሙ የሚሠራቸውን ሥራዎች ሕዝቡ እንዲያውቅ ለማድረግ ከፋና ጋር በትብብር መሥራት አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል ብለዋል።

ዘርፉ ላይ እየተሠሩ ያሉ ሥራዎችን ለሕዝቡ ለማሳወቅ ብሎም ኅብረተሰቡ ጋር የለውን ቅሬታ ለመሥማት እና ተቋሙ ከኅብረተሰቡ የሚፈልጋቸውን ነገሮች ለማሳወቅ ሥምምነቱ ያግዛል ነው ያሉት።

በቀጣይም ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በትብብር ለመስራት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ዝግጁ መሆኑን ነው ያነሱት፡፡

በቅድስት ብርሃኑ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.