Fana: At a Speed of Life!

በዘመናዊ ቴክኖሎጂና ብቃት ባለው የሰው ኃይል አስተማማኝ ተቋም እየገነባን ነው- ሌ/ ጄ ይልማ መርዳሳ

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር ኃይል በዘመናዊ ቴክኖሎጂና ብቃት ባለው የሰው ኃይል እየተደራጀ ያለ ጠንካራና አስተማማኝ ተቋም መሆኑን የአየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄነራል ይልማ መርዳሳ ገለጹ።
የኢትዮጵያ አየር ኃይል በደረጃ-7 የሙያ ማሻሻያ ያደረጉ የአየር ኃይል ነባር አባላትንና አዲስ ከሕብረተሰቡ የተመለመሉ መሰረታዊ ውትድርና ያጠናቀቁ የአየር ኃይል አባላትን አስመርቋል።
 
በመርሐ-ግብሩ ላይ በመገኘት መልዕክት ያስተላለፉት የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄነራል ይልማ መርዳሳ÷ አየር ኃይሉ በዘመናዊ ቴክኖሎጂና ብቃት ባለው የሰው ኃይል እየተደራጀ መሆኑን ገልጸዋል።
 
የኢትዮጵያ አየር ኃይል ከጥንት ጀምሮ ታላቅ ስም ያለው ተቋም መሆኑን ጠቅሰው÷አሁንም ከዘመኑ ጋር እየተራመደ ያለ የሀገር አለኝታ የሆነ አስተማማኝ ተቋም መሆኑን ተናግረዋል።
 
ከዘመኑ ቴክኖሎጂ ጋር የሚራመድ አስተማማኝና የሀገርን የአየር ክልልና ዳር-ድንበር በአስተማማኝ መልኩ መቆጣጠር የሚችል መሆኑንም ጠቅሰዋል።
 
በዛሬው እለት ለምርቃት የበቁት የአየር ኃይል አባላትም በትውልድ ቅብብሎሽ ለሚገነባው ተቋም ተጨማሪ አቅም መሆናቸውንም ጠቁመዋል።
 
ምሩቃኑ በቀጣይ የተቋሙን ባህልና እሴት በመላበስ ለሚቀጥለው የሥልጠና ምዕራፍ እራሳቸውን ማዘጋጀት እንዳለባቸው ማሳሰባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.