Fana: At a Speed of Life!

ርዕሳነ መስተዳድሮችለጥምቀት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ ክልሎች ርዕሳነ መስተዳድሮች ለጥምቀት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ፡፡

የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ርስቱ ይርዳ ባስተላለፉት መልዕክት÷ የጥምቀት በዓል ከሃይማኖታዊ በዓልነቱ ባሻገር የሀገሪቱን መልካም ገፅታ ለመገንባት ፋይዳው የጎላ ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያ በየጊዜው የሚያጋጥሟትን ፈተናዎች በዜጎቿ ጥረት እየተሻገረች ለዚህ በቅታለች ያሉት አቶ ርስቱ÷ አሁን የተገኘውን ዘላቂ ሰላም በማስቀጠል በተሰማራንበት የሥራ መስክ ጠንክረን መሥራት ይጠበቅብናል ብለዋል።

አያቶቻችን በደም እና በአጥንት ያቆዩልንን ሀገር በላባችን ድህነትን ለማጥፋት በመረባረብ ማጽናት የዚህ ትውልድ ድርሻ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

በተመሳሳይ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት÷ የጥምቀት በዓልን ስናከብር በመከባበርና በመተባበር ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡

በዓሉ ከሃይማኖታዊ አስተምህሮው ባለፈ ማኅበራዊና ባህላዊ ፋይዳው ከፍተኛ በመሆኑ÷ ይህንን ሃብት በማክበር፣ በመጠበቅ እና በማልማት በጥንቃቄ መያዝ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

በተሰለፍንበት የሥራ መስክ ሁሉ ከእኛ የሚጠበቀውን ግዴታችንን ልንወጣ ይገባል ብለዋል በመልዕክታቸው፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.