Fana: At a Speed of Life!

በትግራይ ክልል የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ክትባት እየተሰጠ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል የኮቪድ-19 ወረርሽኝ እና ሌሎች መደበኛ ክትባቶች ለህብረተሰቡ እየተሰጡ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
 
በሚኒስቴሩ የእናቶችና ህጻናት ክትባት ዴስክ ሃላፊ መልካሙ አያሌው እንደገለጹት÷ የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ በጤናው ዘርፍ በግጭቱ ጉዳት የደረሰባቸው ተቋማትን ስራ ማስጀመር ጨምሮ በርካት ስራዎች እየተከናወኑ ነው፡፡
 
በዚህ መሰረትም በክልሉ ለኮሮና ቫይረስ እና ለተለያዩ በሽታዎች የሚሰጡ መደበኛ ክትባቶች ወደ ክልሉ መላካቸውን አንስተዋል፡፡
 
አገልግሎቱን የሚሰጡ የዘርፉ የጤና ባለሙዎች ልዑካንም በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች መሰማራታቸውን ነው ያስረዱት፡፡
 
የክትባት ስራውን በሚገባው ፍጥነት ለማሳለጥም ከዩኒሴፍ እና ዓለም ጤና ድርጅት ጋር በቅንጅት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
 
በቅርቡ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረውን የኩፍኝ በሽታ ክትባት በትግራይ ክልል ለማስቀጠልም ክትባቶችን ወደ ክልሉ ለመላክ ዝግጅት መጠናቀቁን ገልጸዋል፡፡
 
ለዚህም ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር አስፈላጊው ውይይት መደረጉን ሃላፊው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡
 
በመላኩ ገድፍ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.