Fana: At a Speed of Life!

የዓለም አቀፉ ቀይመስቀል ኮሚቴ ፕሬዚዳንት አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም አቀፉ ቀይመስቀል ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ሚርጃና ስፖልጃሪክ ኤገር ለሁለት ቀናት የሥራ ጉብኝት ዛሬ አዲስ አበባ ገቡ፡፡

ፕሬዚዳንቷ በቆይታቸው ከመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር እንዲሁም የአፍሪካ ሕብረት መሪዎች ጋር እንደሚወያዩ ይጠበቃል፡፡

በውይይታቸውም÷ በኢትዮጵያ ስላለው የሰብዓዊ ሁኔታ እና የነበረው ግጭት በሀገሪቱ ብሎም በማህበረሰቡ ላይ ስላሳደረው ተፅዕኖ እንደሚመክሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስታውቀዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.