Fana: At a Speed of Life!

የጌዴኦ ብሔረሰብ የምስጋና እና የዘመን መለወጫ በዓል በዲላ ከተማ ተከበረ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 20 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጌዴኦ ብሔረሰብ የምስጋና እና የዘመን መለወጫ በዓል “ያልተበረዘ ባህላዊ እሴት ለዘላቂ ሰላምና ልማት” በሚል በሪ ቃል በዲላ ከተማ ተከብሯል፡፡

“ዳራሮ ለዘላቂ ሰላምና ልማት” በሚል መሪ ቃል የ2015 ዓም የጌዴኦ ብሔረሰብ ዘመን መለወጫ ዳራሮ እና የስጦታ (ጉማታ) ክብረ-በዓል በደመቀ ሥነ -ሥርዓት በጌዴኦ ዞን ዲላ ከተማ ተከብሯል፡፡

የደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳን ጨምሮ የዞን እና የወረዳ አመራሮች ፣ አባ ገዳዎች ፣ የከተማው ህብረተሰብ፣ የአጎራባች ብሄር ብሄረሰብ ተወካዮች በበዓሉ ላይ ታድመዋል።

በዓሉ በአባ ገዳዎች ምርቃት ተጀምሮ÷ በተለያዩ ሁነቶች በድምቀት መከበሩ ነው የተገለጸው።

በኢሳያስ አስራት

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.