Fana: At a Speed of Life!

ለ36ኛው የአፍሪካ ሕብረት ጉባዔ ዝግጅት መደረጉ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ እና 42ኛው የሕብረቱ አስፈፃሚዎች ጉባዔ በፈረንጆቹ ከየካቲት 15 እስከ 19 ቀን 2023 በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

ለጉባዔው በተደረገው ቅድመ ዝግጅት ዙሪያ÷ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የቱሪዝም ሚኒስቴር እንዲሁም 30 ተቋማትን በአባልነት የያዘው የብሄራዊ የዝግጅት ኮሚቴ እና የሆቴሎች ተወካዮች በተገኙበት ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ በመድረኩ ላይ ዝግጅቱን አስመልክተው በሰጡት ማብራሪያ÷ ከፈረንጆቹ የካቲት 14 ጀምሮ እንግዶች ወደ መዲናዋ የሚገቡ በመሆኑ ለሀገሪቷ መልካም ገፅታ በሚመጥን መልኩ እንግዶችን ለመቀበል ልዩና ከፍተኛ ዝግጅት መደረጉን ገልፀዋል።

ሀገሪቷ ከሰላም ስምምነቱ በኋላ የምታስተናግደው ጉባዔ በመሆኑ ለሀገሪቷ መልካም ገፅታ በሚመጥን መልኩ ዘርፈ ብዙ ዝግጅት መደረጉን አንስተዋል፡፡

ሆቴሎች ለጉባዔው የሚመጡ እንግዶችን ሲያስተናግዱ ኢትዮጵያን እና አፍሪካን ታሳቢ ባደረገ መልኩ ድርብ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል::

የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ዳዊት በበኩላቸው÷ ከዚህ ቀደም ከነበረው በተሻለ መልኩ ሆቴሎች እንግዶችን ማስተናገድ እንዲችሉ ከፍተኛ ዝግጅት መደረጉን አንስተዋል።

ኢትዮጵያ ካላት የቱሪዝም ዘርፉ እምቅ አቅም አንፃር ተጠቃሚ ባለመሆኗ የጉባዔውን ዕድል በሚገባ ለመጠቀም ዝግጅት ተደርጓል ነው ያሉት።

በመድረኩ ላይ ከፀጥታ እና ደኅንነት አኳያ የሚመለከታቸው ተቋማት ከፍተኛ ዝግጅት ማድረጋቸው ተገልጿል።

በአዲሱ ሙሉነህ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.