Fana: At a Speed of Life!

በወላይታ፣ጌዴኦና ጎፋ ዞኖች የሕዝበ ውሳኔ ድምጽ አሰጣጥ ሒደቱ በሰላም ተጠናቋል

አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በወላይታ፣ጌዲኦ እና ጎፋ ዞኖች ሲካሄድ የነበረው የደቡብ ኢትዮጵያ ምስረታ የሕዝበ ውሳኔ ድምጽ አሰጣጥ ሒደት በሰላም መጠናቀቁ ተገልጿል፡፡

በወላይታ ዞን ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ ሲካሄድ የነበረው የሕዝበ ውሳኔ ድምጽ አሰጣጥ ሒደት በሰላም ተጠናቆ ጣቢያዎች ለቀጣይ ስራ ዝግጁ መሆናቸው ተመላክቷል፡፡

የዞኑ ሕዝብ ውሳኔ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ምክትል ሃላፊ አቶ ሙሉጌታ ሻንካ÷ በዞኑ በ1 ሺህ 112 የምርጫ ጣቢያዎች የድምጽ አሰጣጥ ሒደቱ በሰላም መጠናቀቁን ተናግረዋል፡፡

በተመሳሳይ በጌዴኦ ዞን የተካሄደው የሕዝበ ውሳኔ ድምጽ አሰጣጥ ሒደት በሰላም መጠናቀቁን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብዮት ደምሴ ገልፀዋል፡፡

በዞኑ ውስጥ በ6 26 የምርጫ ጣቢያዎች የተካሄደው ሕዝበ ውሳኔ በሰላም ተጠናቆ አሁን ላይ የድምጽ  ቆጠራ እየተካሄደ መሆኑን አንስተዋል ።

በጎፋ ዞንም የሕዝበ  ውሳኔ የድምጽ አሰጣጥ ስነ ሰርዓቱ በሰላም መጠናቀቁን የዞኑ አስተዳዳሪ ልዩ አማካሪና የሕዝበ ውሳኔው ተጠሪ  አቶ ብርሃኑ ደቻሳ ገልጸዋል።

በማቱሣላ ማቴዎስ፣ ኢብራሂም ባዲ እና ጥላሁን ሁሴን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.