Fana: At a Speed of Life!

ለወጣት ስራ ፈጣሪዎች በፖሊሲ የተደገፈ የፋይናንስ እገዛ ማድረግ እንደሚገባ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የፋይናንስ ስርዓቱን አካታች በማድረግ ለወጣት ስራ ፈጣሪዎች በፖሊሲ የተደገፈ የፋይናንስ እገዛ ማድረግ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ስራ ፈጣሪ ወጣቶች ማህበር ገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ ስራ ፈጣሪ ወጣቶች ማኅበር ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ”ዘለላ” የተሰኘውን የትስስርና የፖሊሲ አድቮኬሲ የውይይት መድረክ አካሄዷል።

የማህበሩ ፕሬዚዳንት ሳሚያ አብዱልቃድር÷በርካታ የፈጠራ ባለቤቶች የፋይናንስና መሰል ድጋፎችን ባለማግኘታቸው ያሰቡትን ለማሳካት እየተቸገሩ መሆኑን ገልጸዋል።

በተያያዘም ማህበሩ በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮች ላይ ለመስራትና መፍትሔ ለማፈላለግ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱን አመልክተዋል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የኢኖቬሽን ስታርት አፕ ልማት ሊድ ስራ አመራር ሰላምይሁን አደፍርስ በበኩላቸው÷ የፈጠራ ሃሳብ ያላቸውን ዜጎች የሚደግፍ የፋይናንስ ፖሊሲ አለመኖሩ ችግር ሆኖ መቆየቱን ተናግረዋል።

ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት አዳዲስ ሃሳብ ይዘው የሚመጡ ስራ ፈጣሪ ወጣቶችን የሚያስተናግድ የፖሊሲ ማዕቀፍ እየተዘጋጀ መሆኑን ጠቅሰው÷ በቅርብ ጊዜ ስራ ላይ ይውላል ብለዋል።

የፖሊሲ አድቮኬሲ ውይይት ላይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አመራሮች፣ የባንኮች ኃላፊዎችና ባለሙያዎች፣ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ተወካዮች ተሳታፊ መሆናቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.