Fana: At a Speed of Life!

የታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ግንባታ 90 በመቶ መድረሱ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 14 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ግንባታ 90 በመቶ መድረሱ ተገለጸ፡፡

የኅዳሴ ግድቡ የመሠረት ድንጋይ የተጣለበትን 12ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ የግድቡ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽኅፈት ቤት እስካሁን በተሰሩ ሥራዎች እና በቀጣይ ሊሰሩ በታሰቡ ዕቅዶች ላይ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

በመግለጫውም በሀገር ውስጥ እና በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለግድቡ በገንዘብ ፣ በዕውቀት እና በጉልበት አልፎ ተርፎም ግድቡ ያለበትን ዲፕሎማሲያዊ ጫና በመመከት ረገድ በዓለም አቀፍ መድረኮች ያደረጓቸው አስተዋፅዖዎች ተነስተዋል።

በተያዘው ዓመት በቦንድ ሽያጭ ፣ በሥዕል አውደ-ርዕዮችና በሌሎች የገቢ ማሰባሰቢያ መንገዶች ለማሰባሰብ ከታቀደው 2 ቢሊየን ብር 50 በመቶ መሰብሰቡም ተነግሯል።

በቀጣይም የፊታችን መጋቢት 16 ቀን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ 100 ሚሊየን ብር ለመሰብሰብ ያለመ የቦንድ ሽያጭ መርሐ- ግብር እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡

በትዕግስት አስማማው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.