የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ከቱርክ የግብርና ሚኒስትር ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ ከቱርክ የግብርና ሚኒስትር ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸው በውሃ፣ ኢነርጂ እና የሚቲዮሮሎጂ አቅም ልማት ዙሪያ መክረዋል፡፡
ውይይቱ ኒውዮርክ እየተካሄደ ከሚገኘው የተባበሩት መንግስታት የውሃ ጉባኤ ጎን ለጎን የተካሄደ መሆኑን ከኢትዮጵያ ሚቲዮሮሎጂ ኢንስቲትዩት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡