Fana: At a Speed of Life!

መርካቶ አካባቢ የተከሰተውን የእሳት አደጋ መቆጣጠር ተችሏል

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ መርካቶ አካባቢ የተከሰተውን የእሳት አደጋ መቆጣጠር እንደተቻለ የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ገለጸ፡፡

አደጋው ዛሬ ከቀኑ 8 ሰዓት 46 ደቂቃ በክፍለ ከተማው ወረዳ አንድ አደሬ ሰፈር እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በንግድ ሱቆችና መጋዘን ላይ መከሰቱን የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ ንጋቱ ማሞ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።

የእሳት አደጋው በቁጥጥር ስር መዋሉንም አረጋግጠዋል፡፡

የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ውቢት ዲንቃ÷  የእሳት አደጋ ሰራተኞች፣ የፖሊስ አባላትና የአካባቢው ማሕበረሰብ ባደረጉት ርብርብ አደጋው ተስፋፍቶ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ በቁጥጥር ስር ውሏል ብለዋል፡፡

የእሳት አደጋው መንስኤ እንዲሁም በንብረት ላይ የደረሰው የጉዳት መጠን እና ተያያዥ ጉዳዮች በቀጣይ እንደሚገለጽ ተጠቁሟል፡፡

በየሻምበል ምህረት

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.