Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ የመደመር ትውልድ ለሕጻናትና ወጣቶች የስፖርት ማዘውተሪያና መጫወቻ ማዕከል ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች የመደመር ትውልድ ለሕጻናትና ወጣቶች የስፖርት ማዘውተሪያና መጫወቻ ማዕከል ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ተካሄደ፡፡

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 የመደመር ትውልድ ለሕጻናትና ወጣቶች የስፖርት ማዘውተሪያና መጫወቻ ማዕከል ግንባታ ማስጀመሪያ መርሐግብር ተካሂዷል፡፡

በመርሐ ግብሩ ላይ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ባደረጉት ንግግር ÷ በመደመር እሳቤ ትውልዱን በማነጽ በአዕምሮና በአካል በማበልፀግ በሀገሩ የሚኮራ ትውልድ ማፍራት ይገባል ብለዋል፡፡

የመደመር ትውልድን በተግባር ያሳየ የግንባታ መርሐ ግብር በማስጀመር የትናንቱን አስቀጥለን ዛሬን የበለጠ ብሩህ በማድረግ ልጆችን በማስተማርና በመምከር በስፖርትና ሥነምግባር የተካኑ እንዲሆኑ በማስቻል ኃላፊነት አለብን ሲሉ በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡

ከንቲባ አዳነች ለሕጻናት የመደመር ትውልድ መጽሐፍንና የስፖርት ትጥቅ አልባሳት አበርክተዋል፡፡

ቀደም ሲል በአእምሮና በአካል የዳበረ ጠንካራ ትውልድ ለመገንባት በተጀመረው ፕሮጀክት ባለፉት አምስት ዓመታት 394 የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ተገንብተው ለአገልግሎት ክፍት መደረጋቸወን አስታውሰዋል፡፡

ዛሬ ግንባታቸው የተጀመሩ 12 ቦታዎች በቀጣይ ሶስት ወራት ጊዜ ውስጥ ተጠናቅቀው ለሕጻናቱ ክፍት እንደሚደረጉም አመላክተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ ሦስተኛ መጽሐፋቸውን አሳትመው ትውልዱ ሀገሩን የሚወድና የሚያጸና ሆኖ እንዲገነባ ላበረከቱት አስተዋጽዖ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ በላይ ደጀን ፥ በቀጣይ ሦስት ወራት የሚጠናቀቀው ሜዳ ፋት-ሳል÷ እግር ኳስ፣ እጅ ኳስ፣ መረብ ኳስ፣ ቅርጫት ኳስ እና ቮሊቦልና ጠረጴዛ ቴኒስን ማካተቱን አብራተዋል፡፡

እንዲሁም በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በ ‘የመደመር ትውልድ’ መጽሐፍ ሽያጭ ገቢ የሚገነባው የታዳጊ ሕጻናትና የወጣቶች የስፖርት ማዘውተሪያ ማዕከል ግንባታ ማስጀመርያ መርሐ ግብር ተካሂዷል፡፡

የብልፅግና ፓርቲ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሞገስ ባልቻ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በተካሄደው መርሐ ግብር ላይ እንዳሉት÷ ትውልዱ በአካል ብቁ ሆኖ ለየትኛውም ተልዕኮ ዝግጁ እንዲሆን የስፖርት ማዘውተሪያ ቅንጦት ሳይሆን መሠረታዊ ጉዳይ ነው፡፡

በሌላ በኩል በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ከመደመር ትውልድ መጽሐፍ ሽያጭ በተገኘው ገቢ የሕጻናትና ወጣቶች መጫወቻ ሜዳ ግንባታ በይፋ ተጀምሯል፡፡

የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ምክትልና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ዓለማየሁ እጅጉ እንደገለፁት÷ ግንባታው በፍጥነት ተጠናቆ ለታለመለት ዓላማ እንዲውል የነዋሪው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ በባለቤትነት ስሜት መከታተል ይገባል፡፡

ምንጭ፡- የክፍለ ከተሞቹ የኮሙኒኬሽን ጽሕፈት ቤቶች

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.