Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በርካታ ለውጦች ማምጣቱ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በርካታ ለውጦች አምጥቷል ሲሉ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል ተናገሩ፡፡

የንቅናቄው ጉዞና የባለድርሻ አካላት ሚና በሚል የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው፡፡

በመርሐ-ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ ታምርት ሀገር አቀፍ ንቅናቄ ከተጀመረ ጀምሮ ባለፉት ወራት ለውጦች ተመዝግበዋል ብለዋል፡፡

ዘርፋ በሀገር ውስጥና በዓለም አቀፍ የገጠሙትን ጫናዎች በመቋቋም ኢንዱስትሪዎች ወደ ስራ እንዲገቡና የስራ እድል በመፍጠር ውጤት እንዲያመጡ ማስቻሉን ጠቅሰዋል፡፡

ይሁንና አሁንም ግን ዘርፉ መቀናጀት እና በሀላፊነት መስራትን እንደሚጠይቅ ነው ያነሱት፡፡

በመድረኩ ሠነዶች ቀርበው ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ይደረግባቸዋል ተብሎ ይጠበቃል።

በሃይማኖት ወንድራድ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.