Fana: At a Speed of Life!

17ኛው የኢትዮጵያ ዳርት ሻምፒዮና ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ዳርት ፌዴሬሽን አዘጋጅነት ሲካሄድ የቆየው 17ኛው የኢትዮጵያ ዳርት ሻምፒዮና ውድድር ተጠናቀቀ ፡፡

በውድድሩ በሁለቱም ፆታዎች በታዳጊና በአዋቂ በነጠላ፣ በጥንድ፣ በድብልቅ እንዲሁም በቡድን በተደረገ ውድድር አዲስ አበባ በ456 ፣አማራ ክልል በ337፣ደቡብ ክልል በ319 ነጥቦች ከ1ኛ እስከ 3ኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋው አጠናቀዋል፡፡

በውድድሩ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተጫዋቾች  የማጣሪያ ውድድር በማድረግ መስከረም 2016ዓ.ም ለሚካሄደው የአለም የዳርት ሻምፒዮና ላይ በቀጥታ ሀገራቸውን በመወከል ተሳታፊ እንደሚሆኑ ተገልጿል፡፡

በውድድሩ ላይ የኢትዮጵያ ዳርት ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ቢልልኝ መቆያ፣ የፌዴሬሽኑ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ካሳ ተበጀ እንዲሁም የፌዴሬሽኑ ስራ አስፈጻሚ አባላትና የክብር እንግዶች መገኘታቸውን ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.