Fana: At a Speed of Life!

የጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት ለገበታ ለትውልድ ፕሮጀክት ከ1 ነጥብ 2 ቢሊየን ጀምሮ የተለያየ የገንዘብ መጠን ድጋፍ ያደረጉ ተቋማትን አመሰገነ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 27 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት ለገበታ ለትውልድ ፕሮጀክት ከ1 ነጥብ 2 ቢሊየን ጀምሮ የተለያየ የገንዘብ መጠን ድጋፍ ያደረጉ ተቋማትን አመሰገነ።

ፅህፈት ቤቱ ድጋፍ ያደረጉ ተቋማት የመጀመሪያ ዙር ዝርዝርን ይፋ አድርጓል።

በዚሁ መሰረት የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር፣ ኢትዮ ቴሌኮም 1 ቢሊየን ብር፣ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ 500 ሚሊየን ብር ፣ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ 150 ሚሊየን ብር፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል እና ሜድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ 100 ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጋቸውን አስታውቋል።

በተጨማሪም የመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር፣ በግል ድርጅቶች እና ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር 100 ሚሊየን ብር እንዲሁም የኢትዮጵያ ባህርና ሎጅስቲክ አግልግሎት 200 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርገዋል ነው ያለው፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.