Fana: At a Speed of Life!

ቼልሲ ፍራንክ ላምፓርድን ጊዜያዊ አሰልጣኝ አድርጎ ቀጠረ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ የቀድሞ ኮከቡን እና የቡድኑ አሰልጣኝ የነበረውን ፍራንክ ላምፓርድ የክለቡ ጊዜያዊ አሰልጣኝ አድርጎ መቅጠሩን አስታውቋል።

ላምፓርድ ከቸልሲ አሰልጣኝነት ከተሰናበተ ከሁለት አመት በኋላ ተመልሶ እስከ ውድድር አመቱ ማብቂያ ድረስ ቸልሲን ለማሰልጠን ቦታውን ተረክቧል።

ከአሰልጣኝ ፍራንክ ላምፓርድ በተጨማሪ የቀድሞው የቼልሲ ኮከብ አሽሊ ኮል በቼልሲ አስልጣኞች ሰብስብ ውስጥ እንደሚካተት ተገልጿል፡፡

ቼልሲ ላምፓርድን በጊዜያዊ አሰልጣኝነት ቢቀጥርም በቋሚነት ግን ሉዊስ ኤንሪኬን ጨምሮ ከሌሎች አሰልጣኞች ጋር እየተደራደረ መሆኑን የእንግሊዝ ጋዜጦች አስነብበዋል።

የእንግሊዙ ክለብ አሰልጣኝ ግርሃም ፖተርን ከውጤት ቀውስ ጋር በተያያዘ ማሰናበቱ ይታወሳል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.