Fana: At a Speed of Life!

የፕሪሚየር ሊጉ 17ኛ ሳምንት ጨዋታዎችና የሥነ ምግባር ውሳኔዎች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 17ኛ ሳምንት በተደረጉ ጨዋታዎች ሰባት ጨዋታዎች በመሸናነፍና አንድ ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቅቋል፡፡

በተደረጉት ጨዋታዎችም 21 ግቦች በ18 ተጫዋቾች መቆጠራቸው ነው የተገለጸው፡፡

በሳምንቱ 38 ተጫዋቾችና የቡድን አመራሮች በቢጫ ካርድ ሲገሰፁ÷ ሁለት ተጫዋቾች ደግሞ ቀይ ካርድ ተመልክተዋል።

በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል።

በዚህም የኢትዮጵያ ቡናው አማኑኤል ዮሃንስ ሁለተኛ ቢጫ ካርድ የሚያስጥ ጥፋት በመፈፀሙ ቀይ ካርድ አይቶ ከጨዋታ ሜዳ በመውጣቱ 1 ጨዋታ እንዲታገድ ፣ የኢትዮጵያ መድኑ ሀቢብ መሃመድ በተለያዩ አምስት ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ የተመለከተ ሲሆን ÷አንድ ጨዋታ እንዲታገድና 1 ሺህ 500 ብር እንዲቀጣ ተወስኗል፡፡

እንዲሁም የለገጣፎ ለገዳዲ ክለቡ ኮፊ ሜንሰህ ዳኛን አስጸያፊ ስድብ በመሳድብ ቀይ ካርድ አይቶ ከጨዋታ ሜዳ በመወገዱ 3 ጨዋታ እንዲታገድ እና 3 ሺህ ብር እንዲከፍል መወሰኑ ጠተቁሟል፡፡

እንዲሁም ኮፊ ሜንሰህ ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ በቀይ ካርድ ወጥቶ ወደ መልበሻ ክፍል በመሄድ ላይ እያለ የኢትዮጵያን ዳኞችን አስጸያፊ ስድብ በመሳደቡ ከተቀጣው ቅጣት በተጨማሪ ሶስት ጨዋታ እንዲታገድና 3 ሺህ ብር እንዲከፍል ተወስኗል፡፡

ከዚህ ባለፈም የሲዳማ ቡናው አዱኛ ፀጋዬ በቴክኒክ ክልል ውስጥ የሚገኘውን መስታወት በመስበሩ 10ሺህ ብር እንዲከፍል ሲወሰን እንዲሁም የተሰበረውን ንብረት እንዲተካ ወይም አወዳዳሪው አካል የሚያቀርበውን የንብረቱን ዋጋ እንዲከፍል ተወስኗል፡፡

በክለቦች ደረጃ በተላለፈ ቅጣት ደግሞ ኢትዮጵያ መድን በ17ኛ ሳምንት ጨዋታ የክለቡ ደጋፊዎች የዕለቱን ዳኛ አስጸያፊ ስደብ በመሳደባቸው ለፈፀሙት ጥፋት ክለቡ 50 ሺህ ብር እንዲከፍል መወሰኑን የሊግ ካምፓኒው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.