Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በኳታር  በሚካሄደው የዳይመንድ ሊግ ይሳተፋሉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በመጪው ግንቦት ወር  በኳታር ዶሃ በሚካሄደው የዳይመንድ ሊግ ውድድር ይሳተፋሉ፡፡

በአለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና የሪከርድ ባለቤቱ  አትሌት ለሜቻ ግርማ ደግሞ በመድረኩ ሰፊ የማሸነፍ ግምት ተሰጥቶታል፡፡

የኦሎምፒክ እና የሁለት ጊዜ የአለም መሰናክል ሻምፒና የብር ሜዳሊያ አሸናፊው ለሜቻ ግርማ በኳታሩ የ3ሺህ ሜትር የዳይመንድ ሊግ ከአምስት አትሌቶች ከባድ ፉክክር ይጠብቀዋልም ተብሏል፡፡

ከለሜቻ ግርማ በተጨማሪ አትሌት ዮሚፍ ቀጀልቻ እና ሰለሞን ባረጋ በርቀቱ  የሚሳተፉ ሲሆን÷ ሞሮኳዊው ሶፊያን ኤል ባካል እና ኬንያዊው ጢሞቲ ቸሪዮት ሌሎች ተሳታፊ አትሌቶች ናቸው፡፡

ዋንዳ ዳይመንድ ሊጉ ግንቦት 5 በኳታር ዶሃ ሚካሄድ መሆኑን ከአለም አትሌቲክስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.