Fana: At a Speed of Life!

በሀላባ ዞን በተከሰተ የጎርፍ አደጋ የ5 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀላባ ዞን በተከሰተ ከባድ የጎርፍ አደጋ የአምስት ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለጸ፡፡

በዞኑ ዌራ ዲጆ ወረዳ ትናንትና የጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው የጎርፍ አደጋ የአምስት ሰዎች ማለፉን የዞኑ አስተዳደር ገልጿል፡፡

በተከሰተው የጎርፍ አደጋ ህይወታቸው ካለፉት ውስጥ የሶስቱ አስክሬን ሲገኝ፤ የሁለቱ አስክሬስ እስካሁን እንዳልተገኘ ተጠቁሟል፡፡

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙህዲን ሁሴን÷ በቀጣይም ድንገተኛ የጎርፍ አደጋ ሊከሰት ስለሚችል ነዋሪዎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስበዋል።

በተለይም ሕብረተሰቡ የጎርፍ ማፋሰሻ ቦታዎችን ማዘጋጀትን ጨምሮ ሌሎች አስፈላጊ ቅድመ ጥንቃቄዎችን እንዲያደርግ አስገንዝበዋል፡፡

በጎርፍ አደጋው ምክንያት ህይወታቸውን ላጡ እና ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖችም የተሰማቸውን ሀዘን እንደገለጹም የክልሉ ኮሙኒኬሽ መረጃ ያመላክታል፡፡

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.