Fana: At a Speed of Life!

በሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የተከሰተውን የእሳት አደጋ መቆጣጠር መቻሉ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 3 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)በሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ውስጥ የተከሰተውን የእሳት አደጋ መቆጣጠር መቻሉን የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

በሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ውስጥ ከመጋቢት 29 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ እሳት መነሳቱ ይታወቃል፡፡

በብሔራዊ ፓርኩ ውስጥ ግጭ እና እሜት ጎጎ የተነሳውን እሳት የከፋ ጉዳት ሳያደርስ የፓርኩ ሰራተኞች፣ የአካባቢው ማህበረሰብ እና የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላት በጋራ በመረባረብ እሳቱን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር መቻሉ ተገልጿል፡፡

እሳቱ በድጋሚ አገርሽቶ ጉዳት እንዳያስከትልም ጥበቃ እየተደረገለት እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

እሳቱ የተነሳበትን ምክንያት እና ያደረሰውን ጉዳት በተመለከተ የኢትዮጵያ የዱር እንስት ጥበቃ ባለስልጣን በቅርቡ መግለጫ የሚሰጥ መሆኑንም ባለስልጣኑ አስታውቋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.